ቻይና የኮሮና ቫይረስን መነሻ ለሚያጣራ ቡድን በሬ ክፍት ነው አለች

66

አዲስ አበባ  ግንቦት  17/2012 (ኢዜአ)  ቻይና የኮሮና ቫይረስን መነሻ ለማጣራት የሚፈልግ ማንኛውም  የጥናት     ቡድን በሯን ክፍት ማድረጓን ገለጸች፡፡

የምርመራ ሂደቱ የአለም ጤና ድርጅት የሚሳተፍበትና  ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነትም ሆነ   ከፖለቲካዊ ፍላጎት  ነጻ እንዲሆን  አስጠንቅቃለች፡፡

የቻይና  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ዋንግ ዪ  በሀገሪቱ የአመታዊ የፓርላማ መከፈቻ ላይ  እንዳሉት “ከአለም አቀፉ የሳይንስ ማህበረሰብ የኮሮና ቫይረስን መነሻ ማጣራት ለሚፈልግ ቡድን  ቻይና ፈቃደኛ ነች “ ብለዋል፡፡

“ምርመራው ሞያዊ ፣ፍትሀዊና ገንቢ” መረጃዎች  ለህዝብ እንደሚሰጥ እምነት አለኝም  ሲሉ  አክለዋል፡፡

ምርመራው ከፖለቲካኞች ጣልቃ ገብነት፣የሀገራትን ሉአላዊነት የማይጋፋ ማንንም ወንጀለኛ ለማድረግ የማይውል መሆን እንዳለበት በማሳሰብ ፡፡

 በአሜሪካ ፖለቲከኞች  የተከፈተብን የስም ማጥፋት ፕሮፖጋንዳ ቻይናን “ለማግለል”ያለመ ነው ሲሉም ተደምጠዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ  ፡፡

በያዝነው ወር መጀመሪያ  የተባበሩት መንግስታት ጤና ድርጅት የቫይረሱን መንስኤ  እንዲያጠና ለቤጄንግ ያቀረበውን ጥሪ  መቀበል አለመቀበላቸውን በንግግራቸው አላካተቱም ሚስተር ዋንግ  ፡፡

ቀደም ሲል ቻይና የወረርሽኙን መነሻ ለማጣራት በሽታው መቆም አለበት  የሚል አቋም  መያዟን የዘገበው ኤ .ኤፍ.ፒ የዜና ወኪል ነው ፡፡

ይህን ተከትሎም  የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕና የጽህፈት ሚኒስታራቸው ማይክ ፖምፒዮ  ቫይረሱ ከቻይና ላብራቶሪ  የጥንቃቄ ጉድለት መውጣቱን በተደጋጋሚ ሲገለጹም ቆይተዋል፡፡

ባለፉት ሳምንታትም  አሜሪካና አውስትራሊያ የቫይረሱን መነሻ  ምርመራ  እንዲደረግበት  መጠየቃቸውም ይታወሳል ፡፡

 ምንም እንኳ አብዛኞቹ ሳይንቲስቶች ቫይረሱ ከውሀን ግዛት የእንሳሳት ገበያዎች ከእንስሳት ወደ ሰው   እንደተላለፈ ግምታቸውን ቢስቀምጡም፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም