ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ በኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ተገኝተው ሠራተኞችን አበረታቱ

95

አዲስ አበባ ግንቦት 16/2012 (ኢዜአ) ዶክተር አብይ ዛሬ ከጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ ጋር በመሆን ሆስፒታሉን ሲጎበኙ፤ ለእስልምና እምነት ተከታይ የህክምና ባለሙያዎች መልካም በዓል በመመኘት ስጦታ አበርክተዋል።

የጤና ባለሙያዎችና ሠራተኞቹ እያደረጉት ያለውን ጥረት በማድነቅም ‘ወረርሽኙን በሕብረት ከታገልነው እናሸንፈዋለን’ ብለዋል።

የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት በዚያ የሚገኙ ሠራተኞችን የሚታበረታታ እንደሆነ ገልጸዋል።

ሠራተኞቹም የትንሣኤና የዛሬውን የዒድ አልፈጥር በዓል በሆስፒታሉ ውስጥ ማክበራቸውን ተናግረዋል።

ከተለያዩ አካላት ስጦታዎች እየተበረከቱላቸው መሆኑን ገልጸው፤ ትልቁ ስጦታ ግን ለኮቪድ-19 ጥንቃቄ ማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል።

በዓሉን በሆስፒታሉ ውስጥ ያከበሩ የእስልምና እምነት ተከታይ የጤና ባለሙያዎችም በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጉብኝት በዓሉን በደስታ ማክበራቸውን ተናግረዋል።