በኮቪድ-19 የተያዘች አንዲት ኢትዮጵያዊ ነብሰጡር እናት ልጇን በሰላም ተገላገለች

109

አዲስ አበባ ግንቦት 16/2012 (ኢዜአ) በኮቪድ-19 ተይዛ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በሕክምና ላይ የነበረች አንዲት ነብሰ ጡር እናት በሠላም መገላገሏን ሆስፒታሉ አስታወቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ዛሬ ሆስፒታሉን ሲጎበኙ ለእመጫቷ ስጦታ አበርክተውላታል።

የሆስፒታሉ ዋና ስራአስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው በሆስፒታሉ በሕክምና ላይ የነበረችው ነብሰ ጡር እናት ከትናንት በስትያ በቀዶ ህክምና ልጇን በሠላም መገላገሏን ገልጸዋል።

ዶክተር ያሬድ የተወለደው ህፃንና ወላጅ እናት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙም ነው የተናገሩት።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በቫይረሱ ለተያዙ ሰዎች ማገገሚያነት እያገለገለ ያለውን የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሲጎበኙ ለእመጫቷ የተለያዩ ስጦታዎችን አበርክተውላታል።