በኢትዮጵያ ተጨማሪ 61 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

66

አዲስ አበባ ግንቦት 15/2012 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ 3757 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 61 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

በዚህም እስካሁን በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 494 ደርሷል።

ቫይረሱ በምርመራ ከተገኘባቸው 43 ወንዶች እና 18 ሴት ሲሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡

ሚኒስቴሩ እንደገለፀው በዛሬው ሪፖርት 45 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው ናቸው ተብሏል፡፡

በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ከ15 እስከ 70 የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡

በ አዲስ አበባ፤ በቫይረሱ ከተያዙ 48 ሰዎች አመስቱ ቫይረሱ ካለባቸው ጋር ንክኪ የነበራቸው ሲሆኑ 43 ቱ የውጭ ጉዞም ሆነ ፤ በሽታ ካላቸው ጋር ንክኪ የላቸውም።

ከአፋር ክልል ፤ሶስት ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው እና ከዱብቲ ለይቶ ማቆያ ሲሆኑ ሌሎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሰባት ሰዎች ደግሞ ከሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ለይቶ ማቆያ ፤ ከአማራ ክልል ለይቶ ማቆያ የውጭ ጉዞ ታሪክ ያለው አንድ ሰው እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል ሁለት ሰዎች የውጭ ጉዞ ታሪክም ሆነ ከሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው የቡራዩ እና ሰበታ ነዋሪዎች ናቸው፡፡

ተጨማሪ 23 ሰዎች ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ መቶ 151 ደርሷል፡፡በአጠቃላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ ሰዎች 336 መሆናቸውንም ዶክተር ሊያ ገልጸዋል።

እስካሁን በኢትዮጵያ አጠቃላይ 76 ሺህ 962 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም