በኢትዮጵያ ተጨማሪ 14 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

66

ግንቦት 11/2012 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ 3271 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 14 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ይህም እስካሁን በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥርን 365 አድርሶታ።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 11 ወንዶች እና 3 ሴቶች ሲሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። እደሜያቸውም ከ9 እስከ 68 ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

ከአዲስ አበባ በቫይረሱ 9 ከተያዙ ሰዎች መካከል ፤ አንድ የውጭ አገር ጉዞ ታሪክ ያለው፤ 7 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው፤ አንዱ ሰው በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያልነበረው ነውም ተብሏል።

ከሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ለይቶ ማቆያ 3 ሰዎች ; የተቀረውም አንድ ሰው ከትግራይ ክልል ለይቶ ማቆያ የውጭ ጉዞ ታሪክ እንዳለውና አንድ ሰው ከኦሮሚያ ክልል የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ መሆናቸውን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ግልጸዋል፡፡

ተጨማሪ አራት ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ መቶ 120 ደርሷል፡፡

በአጠቃላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ ሰዎች 238 መሆናቸውንም ዶክተር ሊያ ገልጸዋል።

ትናንት በአማራ ክልል ከአጣዬ ሪፖርት የተደረገው አንድ የኮሮና ታማሚ በድጋሚ በመሆኑ ማስተካከያ መደረጉንም ተገልጿል።፡

እስካሁን በኢትዮጵያ አጠቃላይ 62 ሺህ 300 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን እንዲተገብር የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም