የሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች አምባሳደር ጋር ተወያዩ

79

አዲስ አበባ  ግንቦት  3/2012  (ኢዜአ) የሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ በኢትዮጵያ ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች አምባሳደር ጋር ዛሬ ተነጋገሩ። 

ሚኒስትሯ አምባሳደር መሐመድ ሳሊም አል-ራሺድ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ያደረጉት ውይይት ኮቪድ-19 የሚያስከትለውን ቀውስ በመከላከል ላይ ያተኮረ ነበር።

ቫይረሱ በሴቶች  በኢኮኖሚው መስክ ላይ ያላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት  በሚያሳድረው ጉዳዮች  ላይ መወያየታቸውን ሚኒስቴሩ ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ኤምባሲው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ቤተሰቦችን ማዕድ የማጋራት (የማስፈጠር)መርሐ ግብር ያካሄደ ሲሆን፣ ለ200 አባወራዎች የምግብ ድጋፍ አድርጓል።

በቀጣይም የንጽህና መጠበቂያዎች ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን  በመግለጫው ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም