የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በአዳማ የሚገኘውን የፅኑ ህሙማን የህክምና ማእከል ጎበኙ

72

 አዲስ አበባ፤ ግንቦት 1/2012 (ኢዜአ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በአዳማ ከተማ ለኮቪድ 19 የፅኑ ህሙማን የህክምና ማእከልነት የተዘጋጀውን ጎበኙ።

ለኮሮናቫይረስ ህክምና የሚያገለግል በአዳማ ሆስፒታል ቅጥር ጊቢ ውስጥ 150 ዓልጋዎችን የሚይዝ ማእከል ተዘጋጅቷል።

ከእነዚህ አልጋዎች መካከልም 12ቱ አልጋዎች ለፅኑ ህሙማን መከታተያነት የሚያገለግሉ ናቸው።

ይህንን ማእከል የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ ማለዳ በአዳማ ከተማ በመገኘት ጎብኝተዋል።

ሚኒስትሯ በከተማ አስተዳደሩ የተዘጋጀውን የአስገድዶ ለይቶ ማቆያ ማእከልም ጎብኝተዋል።

በመቀጠልም በሞጆ ከተማ በመገኘት ለለይቶ ማቆያነት የተዘጋጁትን ማእከላት እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።

ከዶክተር ሊያ በተጨማሪ ሌሎች የሚኒስቴሩ ከፍተኛ ሃላፊዎች በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም