ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ደም ለገሱ

104

ሚያዚያ 14/2012(ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ዛሬ ጠዋት ደም ለገሱ ፡፡

የደም ልገሳውን ያደረጉት የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ያቀረቡትን ጥሪ በመቀበል መሆኑም ተገልጿል።

የጤና አገልግሎት ስርዓት ኮቪድ-19 ያስከተለውን የጤና ቀውስ ለመቀልበስ በሚረባረቡበት በዚህ ወቅትም፣ የካንሰር ሕሙማን፣ በማዋለጃ የሚገኙ እናቶች እንዲሁም በልዩ ልዩ አደጋ ምክንያት ብዙ ደም የፈሰሳቸው ግለሰቦች በሕይወት ለመቆየት የደም ልገሳ ያስፈልጋቸዋል፡፡

በመሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በዛሬው እለት ደም መለገሳቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በፌስቡክ ገፁ ይፋ አድርጓል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክትም "በተጋረጠብን የኮቮድ 19 ቀውስ ውስጥ አሁንም ደም የሚያስፈልጋቸውና የተለያየ የጤና እክል ያለባቸው ወገኖች አሉ ፡፡ ደም በመለገስ ሕይወት ይታደጉ፡፡ አንድ ላይ ሆነን ሁሉንም መሰናክሎች ማሸነፍ እንችላለን" ብለዋል።፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከዚህ በፊትም ደም መለገሳቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም