የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል

483

ሚያዚያ 1/2012( ኢዜአ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል።

ምክር ቤቱ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው ልዩ ስብሰባው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላት ለመሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለኮሮና ቫይረስ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ፕሮጄክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት አስመልክቶ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያፀድቃል፡፡

ትላንት የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተግባራዊ እንዲሆን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ መጽደቅ ስላለበት ነገ በሚኖረው 2ኛ ልዩ ስብሰባ ምክር ቤቱ የቀረበውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

በልዩ ስብሰባው እነዚህና ሌሎችም አለም አቀፍ ስምምነቶች ረቂቅ አዋጆችን ምክርቤቱ ቤቱ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል፡፡