የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ተማሪዎች በያሉበት ሆነው ትምህርታቸውን የሚከታተሉበት አማራጭ ማዘጋጀቱን ገለጸ

98

መጋቢት 29/2012 ኢዜአ  በኮሮና ቫይረስ  ትምህርት ቤቶች ቢዘጉም ተማሪዎች ባሉበት ትምህርታቸውን የሚከታተሉበትን አማራጭ ማዘጋጀቱን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። 

ቢሮው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን መደበኛ ትምህርት በሚቀጥለው ሳምንት ተማሪዎች  በቤታቸው ሆነው የሚማሩበትን  የተለያዩ አማራጮች ለመግበር ዝግጅት ማጠናቀቁን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

በክልሉ በ16 ሺህ ትምህርት ቤቶች 10 ነጥብ 6 ሚሊዮን ተማሪዎች እና 200 ሺህ መምህራን ይገኛሉ።

በዚህም ተማሪዎቹ በሬዲዮ፣ በፕላዝማ፣ በሳታላይት እና በክልሉ ትምህርት ቢሮ ገጽ ቴሌግራም ቻናል አማራጮች ማግኘት እንደሚችሉ ነው የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ ያስታወቁት።

ቢሮው አማራጮችን ቢያዘጋጅም ወረርሽኙ ሲያልፍ ትምህርት ቤቶች መከፈታቸው ስለማይቀር መምህራኑ አማራጮቹን ተጠቅመው ከወዲሁ መመዘኛዎችን እንዲያጠናቅሩ አሳስበዋል።

ተማሪዎቹ ከቤት ባለመውጣት ራሳቸውን እንዲጠብቁና በበጎ ፈቃድ ስራው የሚሳተፉም ራሳቸውን ጠብቀው ቢሮው በሚያስቀምጠው አቅጣጫ እንዲሆን አስጠንቅቀዋል።

በዚህ አቅጣጫ መሠረት ዘርፉን የሚመራ አነስተኛ ግብር ሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑንም ቢሮው ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም