አገር አቋራጭ አውቶቡሶች በአዲስ አበባ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበ

272

መጋቢት 29/2012 ኢዜአ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር የአገር አቋራጭ አውቶቡስ ባለንብረቶች በመዲናዋ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበ።

የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ሲባል የትራንስፖርት አሠራር ላይ የከተማ አስተዳደሩ የማሻሻያ ውሳኔዎችን በትናንትናው እለት አስተላልፏል።

በውሳኔው መሰረት ታክሲ፣ ሀይገር ባስ፣ መለስተኛና አነስተኛ ህዝብ ማመላለሻዎች በወንበር ከመጫን አቅማቸው በ50 በመቶ እንዲቀንሱና ቀድሞ ከነበረው ታሪፍ በእጥፍ ተሳፋሪዎች እንዲከፍሉ ተብሏል።

ከብዙሃን ትራንስፖርት በስተቀር ከነገ ጀምሮ ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት ከ12 እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ ብቻ እንዲሰራም ተወስኗል።
በመሆኑም ውሳኔውን ተከትሎ በቂ የትራንስፖርት አቅርቦት እንዲኖር የአገር አቋራጭ አውቶቡስ ባለንብረቶች ተሳትፎ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አመልክቷል።

ፍላጎት ያላቸው የአውቶቡስ ባለንብረቶች በሙሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ባለስልጣን በግንባር በመምጣት ሪፖርት እንዲያደርጉና ስምሪት ወስደው ወደ ስራ እንዲገቡ ጥሪ መቅረቡን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም