ከሦስት ሚሊዮን ዓመታት በፊት የኖሩት ሉሲይ ረዝም የልጅነት ጊዜ ነበራቸው

144

መጋቢት 29/2012 ከሦስት ሚሊዮን ዓመታት የነበሩት በኢትዮጵያ በተገኙት አውስትራሎፒተከስ አፋረንሲስ (ድንቅነሽ)ረዘም ያለ የልጅነት ጊዜ  እንደነበራቸው አዲስ ጥናት አመለከተ፡፡  

እነሉሲ በመጀመሪያ የጭንቅላት መጠናቸው ከቺምፓንዚዎች ጋር የሚቀራረብ ቢሆንም በሂደት ቅርጹ ወደ ሰው ልጆች እየተጠጋ እንደመጣም በጥናቱ ተጠቅሷል።

ባልተለመደ ሁኔታ የሌሎች የጥንተሰብ ዝርያዎች ትልቅ አንጎል ይዞ መገኘት የረጅም ጊዜ የጭንቅላት እድገት ውጤት አለመሆኑን ይህ ግኝት ማሳየቱን በሳይንስ አድቫንስስ ጥናት ላይ የተገልጿል ።

ላለፉት 20 አመታት ሲደረጉ የነበሩ ምርምሮችም ያሳዩት ነገር ከ2.5 ሚሊየን አመታት በፊት የነበሩት የጥንተሰብ ዝርያዎች ቆመው የሚራመዱ መሆናቸው የመውለድ ሂደታቸውን ቀለል እንዳደረገላቸውም ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል።

በተቃራኒውየምስራቅ አፍሪቃዎቹ የእነሉሲ ከፊል አፅም አወቃቀር እንደሚያሳየው ከሆነ የጭንቅላት መጠናቸው አሁን ካለው የሰውልጅ መጠን አንጻር ሲሶውን ብቻ እንደያዙ ያብራሩት በጀርመን ሌፕዚሽ የማክስ ፕላንክ ጥንተሰብ ተቋም ተመራማሪዎቹ ፊሊፕ ጉንዝና ባልደረቦቻቸው ከ3 እስከ 4 ሚሊየን አመታት እንዳስቆጠሩ የሚገመቱት  እነሉሲ ቢሆኑም 2.8 ሚሊየን አመታት በማስመዝገብ የዘመናዊ ሰው ዝርያ የሚባለው የአንጎል እደገት የጀመረው ከውልደቱ በሁዋላ መሆኑን አስረድተዋል

እድሜያቸውን ለመገመትና የአነጎል እድገት ሂደታቸውን ለማወቅ በጣም ጥቂት ቁጥር ያላቸው የአውስትራሎፒተከስ አፋረንሲስ ዝርያዎች ላይ ብቻ ጥናት እንደተደረገ ያብራሩት ተመራማሪው የያኔዎቹ የሁለት ወይም የሶስት አመት ጎልማሳ ጎሪላዎችና ቺምፓንዚዎች ያላቸው የአንጎል መጠን ከዛሬዎቹ የ5 አመት የሰው ልጆች ህጻናት ጋር ተቀራራቢ ነበር ብለዋል።

በአዲሱ ጥናት ውስጥ ጉንዝ እና የስራ ባልደረቦቻቸው ዕድሜያቸው ሁለት አመት ከ5 ወር የሚሆኑ ስድስት የአፋረንሲስ አዋቂዎችና ሁለት ህጻናትን በመውሰድ በሰሩት ግምት መሰረት የአውስትራሎፒተከስ ህጻናት ከወላጆቻቸው ያነሰ እንዲሁም ከሰው ልጆች ህጻናት  ጋር የተቀራረበ የአንጎል መጠን እንደነበራቸው አስረድተዋል።

በጥናቱ ባይሳተፉም አዲሱን መረጃ ተመልክተው ከአዋቂዎቹ ጋር ሲነጻጸር ለሉሲ ዝርያዎች ከሰው ልጆች ሕፃናት አቻ በሆነ መልኩ ያነሰ የአንጎል መጠን እንደነበራቸው ያስረዱት በኒውዮርክ ዛሳር ኮሌጅ የጥንተሰብ ስነህይወት ተመራማሪው ዛካሪ ኮፍራን  ውጤቱ የአውስትራሎፒተከስ የአንጎል እድገት በጣም ረጅም ጊዜ የወሰደ መሆኑን አመላካች ነው ብለዋል።

ከልደት በኋላ ያለው ረጅም የህጻናቱ የአንጎል እድገት የአፋረንሲስ እናቶች ልጆቻቸውን የመንከባከብ ጫና የቀነሰላቸው መሆኑን ያስረዱት ጉንዝ ክስተቱ የሰው ልጆችም የተራዘመ የልጅነት ጊዜ እንዲኖራቸው መነሻ ሊሆን እንዳስቻለ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

ከኢትዮዽያ በተገኙት በሁሉም የሉሲ ዝርያዎች ላይ በተደረገ የባለ ሶስት አውታር (3d)ሲቲ ስካን  ምርመራ የህጻናቱን የጥርሶች የራስቅል እና የአንጎል አወቃቀር  ለማወቅ እንዳስቻለ ተገልጻል።

የምርምሩን ውጤት አሳማኝ ሆኖ እንዳገኙት የተናገሩት በአትላንታ ኤሞሪ ዩኒቨርሲቲ የጥንተሰብ ኒውሮ ሳይንቲስቱ ቶድ ፕሪየስ በበኩላቸው በሃዳር የተገኙት የጭንቅላት አጥንቶች ብዙ ነገሮችን የሚያሳዩና ከ2.8 ሚሊዮን ዓመታት በፊት ከነበረውና በደቡብ አፍሪካ ከተገኘው አጥንት ጋር ተመሳሳይነት አላቸው ብለዋል።

የአንጎል እድገትን በሚመለከት አሁንም ጥናት የሚፈልጉ በርካታ ጉዳዮች መኖራቸውን የሚገልጹት በለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የጥንተሰብ ተመራማሪዋ አይዳ ጎሜዝ ሮብልስ በበኩላቸው ጥናቱ ከልጅነት እስከ ጉልምስና ያለውን የአፋረንሲስ ዝርያዎች የአንጎል እድገት ደረጃዎችና ሂደቶች ማሳየት የተሳነው በመሆኑ ሙሉ ነው ተብሎ ሊወሰድ አይችልም ብለዋል።

የእነሉሲን እድገት በሚመለከት የሚሰሩ ጥናቶች አሁንም አወዛጋቢነታቸውን የሚቀጥሉ መሆኑን ያነሳው ድረገጹ ለጥንተ ሰብ ጥናት አንድ አይነት የምርምር ስርአት መከተል ብቻውን በቂ አለመሆኑን አመላካች ነው ብሏል ሲል ሳይንስ ኒውስ ድረገጽ አስነበቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም