ኤስ ቪ ኤስ የአዮዳይዝድ ጨው ማቀነባበሪ ፋብሪካ ለአፋር ኮሮና ቫይረስ መከላከል 5 ሚሊዮን ብር ለገሰ - ኢዜአ አማርኛ
ኤስ ቪ ኤስ የአዮዳይዝድ ጨው ማቀነባበሪ ፋብሪካ ለአፋር ኮሮና ቫይረስ መከላከል 5 ሚሊዮን ብር ለገሰ
ሰመራ መጋቢት 28 /2012 (ኢዜአ) በአፋር ክልል የሚገኘው ኤስ ቪ ኤስ የአዮዳይዝድ ጨው ማቀነባበሪ ፋብሪካ ለክልሉ የኮሮና ቫይረስ መከላከል ስራ የ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለክልሉ ርዕሰ-መስረዳድር አስረከበ ።
ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል በሚችለው ሁሉ እንዲረባረብ የአፋር ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አወል አርባ ጥሪ አቅረበዋል::
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት የአፋር ክልላዊ መንግሰት የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚያስፈልጉ የተለያዩ አደረጃጀቶች አስከ ታችኛው የአስተዳደር እርከን ድረስ በማዋቀር በከፍተኛ ትኩረት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህን ስራ ለመደገፍ መንግሰት ከሚያደርገው ጥረት ጎን ለጎን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በተለይም የሃይማኖት አባቶች ፣ የጎሳ መሪዎች ፣ ወጣቶችና ባለሃብቶች ህብረተሰቡን ከተደቀነበት የበሽታ ስጋት ለመታደግ ከፍተኛ ሃላፊነት አለባቸው ብለዋል ።
የተለያዩ የግል ባለሃብቶች የክልሉን መንግሰት ለመደገፍ ከፍተኛ ተነሳሽነት ያሳዩ ሲሆን የኤስ ቪ ኤስ ጨው ማቀነባባሪያ ፋብሪካ በቁሳቁስና በጥሬ ገንዘብ ያበረከተው የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የዚህ መሳያ መሆኑን ተናግረዋል ።
የኤስ ቪ ኤስ ፋብሪካው ተወካይ አቶ አይናዲስ በቀለ በበኩላቸው በሀገራቱ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል መንግስት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል ።
በሽታው ህብረተሰቡን ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳያደርስ የመከላከሉ ስራ እንደኛ አይነት ደህ ሀገሮች ላይ የሚስከትለው የምጣኔ-ሃብትና ማህበራዊ ቀውስ የከፍ ሊሆን ስለሚችል የመንግስት በጀት ብቻ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም የበኩሉን ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል ።
በዚህ መሰረት የኤስ ቪ ኤስ ጨው ማቀነባባሪ ፋብሪካ ለአፋር ክልላዊ መንግሰት 3 ሚሊዮን ብር የሚገመት ለኮሮና ቫይረስ መከላከል ስራ የሚውል ቁሳቁስና 2 ሚሊዮን ብር ጥሬ ገንዘብ መለገሱን ገልፀዋል ።
የአፋር ክልል ጤና ቢሮ ተወካይ አቶ ሁሴን መሃመድ እንዳሉት ደግሞ በክልሉ ባለፉት 2 ወራት በ7 ሆስፒታሎች የኮሮና ቫይረስ ህክምና መስጫ ማእከላት በማደራጀት ከ5 ሺህ በላይ ሰዎችን ማስተናገድ በሚችሉበት ደረጃ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል