3 ግለሰቦች የመድሃኒትና ምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን ሰራተኞች ነን በማለት በማጭበርበር ገንዘብ ለመቀበል ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ

218

መጋቢት 26/2012(ኢዜአ) ሶስት ግለሰቦች የመድሃኒትና ምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን ሰራተኞች ነን በማለት ሲያጭበረብሩ እና ገንዘብ ለመቀበል ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ፡፡

ተጠርጣሪዎች ወንጀሉን ሲፈፅሙ የተያዙት መጋቢት 23/2012 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በአንድ ግለሰብ ምግብ ቤት ውስጥ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከቅርብ ቀናት ወዲህ የመዲናዋ ነዋሪዎች ዓለም አቀፍ ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ወረርሽኝን ለመከላከል እየታተሩ ይገኛሉ፡፡

ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ ባልተገባ ሁኔታ የግል ጥቅማቸውን ለማካበት አንዳንድ በማጭበርበር ስራ ላይ የተሰማሩ አሉ፡፡

የማጭበርበር ወንጀል የተፈጸመበት ሆቴል ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ዘይነብ ሸምሱን ስለወንጀሉ አፈፃፀም  በሰጡን ምላሽ ተጠርጣሪዎቹ ከልደታ ክፍለ ከተማ የመድሀኒት እና ምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን እንደመጡ እንደገለጹላቸው ተቅሰዋል፡፡

በመቀጠልም ምግብ ቤቱ ፅዳት ይጎድለዋል፣ በዚህ ፅዳቱ ባልተጠበቀ ቤት እንዴት ትሰራላችሁ? ስለዚህ እናሽገዋለን፤ወይም በገንዘብ እንደራደር ሲሏቸው የግል ተበዳይም በመጠራጠር ወደቤታቸው በመግባት ለሚመለከተው አካል ደውለው ከተቋሙ ያልተላኩ መሆኑን በማረጋገጥ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርገዋል፡፡

በአዲስ አበባ የመድሃኒትና ምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን የጤና ተቋማት  ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ሁንዱማ በሰጡን አስተያየት ተጠርጣሪዎቹ በዚህ አሳሳቢ እና በጭንቅ ወቅት መልካም ነገር ማድረግ ሲገባቸው እንደዚህ አይነት እኩይ የማጭበርበር ተግባር ላይ መገኘት እጅግ አሳፋሪ ነው ብለዋል፡፡

የልደታ ክፍለ ከተማ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ፅህፈት ቤት ሃላፊ  አቶ ፍቃዱ ዮሐንስ እንዳብራሩት ያልሆኑትን ነን በሚል በተለያዩ ዘዴዎች የሚያጭበረብሩ ግለሰቦች ሊኖሩ እንደሚችሉ በመገንዘብ ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ካሉ በኋላ አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥማቸው ለፀጥታ አካላት በመጠቆም የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡

የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል እና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ታምራት አለማየሁ በተጠርጣሪዎች ላይ ባደረጉት ምርመራ ከገቢዎች የተፃፈ ሰነድ መያዛቸውን ገልፀው ወደፊት የሚያጣሩት መሆኑን በመጥቀስ ህብረተሰቡ እንደዚህ አይነት አስመሳዮች ሲያጋጥሙት መታወቂያ ማየትና ለሚመለከተው አካል ደውሎ ማሳወቅ አለበት ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወቅታዊ የሆነው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪዲ-19) ወረርሽኝን ለመከላከል በሚደረገው ሁሉ አቀፍ ጥረት የሚዘናጉ፤ ሰዎችን ለማታለልና ለማጭበርበር የሚጥሩ፤ በእኩይ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች አይጠፉምና እንደዚህ