ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ የኮሮናቫይረስ ግንዛቤ አስጨበጡ

79

አዲስ አበባ መጋቢት 23/2012  (ኢዜአ) የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር ፊልሰን በአዲስ አበባ ከተማ በመዘዋወር ስለ ኮሮናቫይረስ የግንዛቤ ማስጨበጥ ተግባር አከናውነዋል።

ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት ባስተላፉት መልዕክት ''ዜጎች አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ባለመጨባበጥ፣ እጅን በመታጠብና የግል ንጽህናን በመጠበቅ ዜጎች ራሳቸውን ከኮሮናቫይረስ መጠበቅ ይገባቸዋል'' ብለዋል።

በተለይም የጤና ባለሙያዎች የሚያስተላልፉትን መልዕክት በሚገባ መተግበር አስፈላጊ እንደሆነም አመልክተዋል።

ቫይረሱ ካለው የስርጭት ባህሪይ አንጻር ሰዎች አለመጨባበጥ፣ ርቀትን መጠበቅና ንክኪን ማስወገድ ወሳኝ እንደሆነም አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታትና ለመከላከል ሁሉም አካል የበኩሉን ድርሻና ሃላፊነት እንዲወጣ ወይዘሮ ፊልሰን ጥሪ አቅርበዋል።

የተለያዩ ሚኒስትሮች ስለኮሮናቫይረስ መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ግንዛቤ የማስጨበጫ ስራ እያከናወኑ እንደሆነ ይታወቃል።

ዛሬ ከቀትር በፊት የንግድና የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በመርካቶ አካባቢ በመዘወዋወር የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ማከናወናቸው የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም