በአዳማ ከተማ በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረው ከነበሩት ውስጥ 29 ሰዎች ነፃ መሆናቸው ተረጋገጠ

136

አዳማ ፣ መጋቢት 22/2012 (ኢዜአ) በአዳማ ከተማ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘበት ግለሰብ ጋር ንክኪ ነበራቸው ተብለው ከተጠረጠሩት ውስጥ 29 ሰዎች ከቫይረሱ ነፃ እንደሆኑ መረጋገጡን የከተማዋ አስተዳደር ጤና መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው ኃላፊና  የኮሮና ቫይረስ መከላከል ግብረ ኃይል አባል የሆኑት ወይዘሮ ሳሚራ ሙሐመድ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው የተረጋገጠው ተጠርጥረው ምርመራ ከተደረገላቸው  42 ሰዎች ውስጥ  ነው።

ከቫይረሱ ነፃ የሆኑት ሰዎች ሙሉ በሙሉ ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ ለቀጣዩ 14 ቀናት በለይቶ ማቆያ ክትትል እንደሚደርገላቸው ተናግረዋል።

ከግለሰቡ ጋር ንክኪ የነበራቸው ቀሪዎቹ ሰዎች  በምርመራ ላይ እንደሚገኙና ውጤታቸውንም እየተጠባበቁ መሆናቸውን   ወይዘሮ ሳሚራ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም