እንግሊዝ በኮሮና ቫይረስ ሐሰተኛ መረጃ ተቸግሬአለሁ አለች

84

መጋቢት 21/2012 እንግሊዝ በኮሮና ቫይረስ ሐሰተኛ መረጃ መቸገሯን ገለጸች፡፡

እንግሊዝ በኮሮና ቫይረስ ሐሰተኛ መረጃ በህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ማህበራዊና የጤና ጉዳት ተከታትሎ የሚያርም ግብረ ሃይል መቋቋሙም ተነግሯል፡፡

በእንግሊዝ ከኮሮና ቫይረስ ጋር የተያያዙ ሐሰተኛ መረጃዎችና ጎጂ መልዕክቶች  በማህበራዊ ሚዲያ በመሰራጨታቸው የብዙዎችን ህይወት አደጋ ላይ እንደጣለ እየተነገረ ነው፡፡

የአገሪቱ የባህል ሚኒስትር ኦሊቨር ዶውደን ለቢቢሲ እንደገለጹት በቫይረሱ ዙሪያ የሚወጡ ሀሰተኛ መረጃዎች፣ አሉባልታዎች እንዲሁም መልዕክቶች የብዙ ሰዎችን ሕይወት ሊያሳጡ ስለሚችል እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ሆኗል፡፡

ባሳለፍነው ሐሙስ መንግስት በቤታችሁ ቆዩ የሚል የጽሁፍ መልዕክት በተላከበት ቅጽበት ሰዎች ለጉዳዩ ትኩረት እንዳይሰጡ በማህበራዊ ሚዲያዎች መልዕክቶች ሲተላለፉ እንደነበር  ያነሱት ሚኒስትሩ፣ ህብረተሰቡም በሀሰተኛው መረጃ የተነሳ  ትዕዛዙን ተግበራዊ እንዳላደረጉም ጠቅሰዋል፡፡

ከዚሁ ጎን ለጎን የሀሰተኛ  ባለሙያዎችን ዋቢ በማድረግ የቫይረሱን መተላለፊያና ሌሎች መረጃዎች  በኦን ላይን መለቀቃቸው እየጨመረ መምጣቱንም   ሚኒስተሩ እንስተዋል፡፡

ሀሰተኛ መረጃዎችና አሉባልታዎች ወደ ህብረተሰቡ በቀላሉና በፍጥነት እንደሚሰራጩ በመጥቀስ፡፡

ሰዎች መረጃዎችን በጥንቃቄ እንዲመረምሩ ለማስቻል ‹‹Don't Feed the Beast›› ወይም አውሬውን አይመግቡ የሚል ዘመቻ መንግሥት መጀመሩን ዶውደን አስታውቀዋል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ፌስቡክ ጎግል፣ ማይክሮሶፍት እንዲሁም ሬዴት ከመንግሥት ጋር ሃሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ያስነበበው ቢቢሲ ነው

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም