በትግራይ ደቡባዊ ዞን 42 የንግድ ሱቆችና 58 የመዝናኛ ቦታዎች ተሻጉ

54

ማይጨው መጋቢት 19/2012 (ኢዜአ) በትግራይ ደቡባዊ ዞን በሸቀጦች ዋጋ ላይ የተጋነነ ጭማሪ ያደረጉና ምርት የደበቁ 42 የንግድ ቤቶች መታሸጋቸውን የዞኑ ከተማ ልማት ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ ገለፀ ። 

የዞኑ ከተማ ልማት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ ሀላፊ  አቶ አታክልቲ ፀጋይ ለኢዜአ እንደተናገሩት የኮሮና ቫይረስ በአገሪቱ መከሰትን ተከትሎ በፍጆታ እቃዎች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት የሚከታተል ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ስራ ጀምሯል።

ግብረሀይሉ የኮሮና ቫይረስ መከሰትን  እንደምክንያት በመጠቀም በሸቀጦች ላይ ዋጋ የጨመሩና ምርት የደበቁ 42 የንግድ ቤቶች እንዲታሸጉ አድርጓል ።

በተጨማሪም ለኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት ይሆናሉ የተባሉ 58 የጫት ፣ የመጠጥ ፣የፑል  ቤቶችን  የሚገኙበት  58 የመዝናኛ ስፍራዎች እንዲዘጉ ተደርጓል ።

ግብረ ሀይሉ የማሸግ እርምጃ የወሰደው በአላማጣ፣ በኮረምና በማይጨው ከተሞች  መሆኑን አስረድተዋል።

ነጋዴዎች አንድ ኩንታል ነጭ ጤፍ ከ3 ሺህ 400 ብር ወደ 4ሺህ ብር የአንድ ኪሎ ግራም በርበሬ ዋጋ ደግሞ ከ75 ብር ወደ 200 ብር  ከፍ እንዲል በማድረግ አለአግባብ ሀብት ለማግበስበስ የሞኮሮ ናቸው ተብሏል ።

በአላማጣ ከተማ ጥፋታቸውን አምነው ይቅርታ የጠየቁ አምስት ነጋዴዎች ደግሞ በማስጠንቀቂያ ስራቸውን እንዲቀጥሉ መደረጉን ከመምሪያ ኃላፊው ገለፃ  ለማወቅ ተችሏል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም