የኢጋድ አባል አገራት የኮቪድ 19 ሥርጭት በጋራ ለመግታት ተስማሙ

64

አዲስ አበባ መጋቢት 16/2012 የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) አባል አገራት የኮቪድ-19 ሥርጭት በጋራ ለመግታት መስማማታቸውን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ።

ኢጋድ እንደ አንድ ቀጣናዊ አሐድ የኮሮናቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት እና የሚያስከትለውን የኢኮኖሚ መሰናክል በውጤታማነት ለመከላከል ቁልፍ የመሪነት ሚናን ለመጫወት እንደሚችል ጠቅላይ ሚንስሩ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሀምዶክ፣ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት መሀመድ አብዱላሂ፣ ከጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ዑመር ጊሌ፣ ከኬኒያው ፕሬዚዳንት ኡኹሩ ኬንያታ እና ከደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ጋር በስልክ ተወያይተዋል።

በነበራቸው የስልክ ውይይትም የኮሮናቫይረስን ላይ በጋራ ለመሥራት መስመማማታቸውን የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

መሪዎቹ ለአዳዲስ እና ፈታኝ ሁኔታዎች ተገቢ ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል፣ በቅርበትና በጋራ ለመሥራት መስማማታቸውም ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ "ከተባበርንና በጋራ ሆነን የቀጣናውን ፍላጎት ለማስጠበቅ አመራሩ ከሠራ፣ የቀጣናዊ ቅንጅት ግባችን አይስተጓጎልም" ማለታቸውም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም