የአድዋን ታሪክ የሚዘክር ዓመታዊ ዓለም አቀፍ ሽልማት ሊካሄድ ነው

111

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 15፣ 2012 (ኢዜአ) የአድዋን ታሪክ የሚዘክር ‘’ዓለም አቀፍ የአድዋ ሽልማት’’ በሚል ስያሜ ዓለም አቀፍ ሽልማት በየዓመቱ ሊካሄድ ነው።

ሽልማቱ ''ኢንተርናሽናል ክላይሜት ቸንጅ ኢንድ ስፖርት ኦተሃ'' በተባለ ሀገር በቀል ድርጅት የተዘጋጀ ሲሆን በተለያዩ መስኮች ጉልህ አስተዋፆ ያበረከቱ ግለሰቦች ይሸለሙበታል።

በሳይንስና ምርምር፣ በፖለቲካ፣ በመዝናኛ፣ በጥበብና አርት፣ በፈጠራ ስራ በፍልስፍና እንዲሁም ሌሎች ዘርፎች ለዓለም ህዝብ ትልቅ ስራ የሰሩትን ሽልማቱ ያካትታል።

ከድርጅቱ መስራቾች አንዱ አትሌት ሙልዬ እያዩ እንደገለፀው ሽልማቱ ዓለምአቀፋዊ ሲሆን ኢትዮጵያዊንና ኢትዮጵያዊያን ያልሆኑ ግለሰቦችን ጭምር አወዳድሮ ይሸልማል።

ሽልማቱ የሚዘጋጀው በአድዋ ድል ስም ሲሆን በየዓመቱ የአድዋ የድል ቀን መታሰቢያ እለት የሚከወን ይሆናል።

አድዋ ዓለም ጥቁሮች ህዝብ የድል መታሰቢያ በመሆኑ ዝግጅቱ ድሉን ለመዘከርና ለዓለም ህዝቦች የበለጠ እውቅና እንዲኖረው ለማድረግ ነው ብሏል።

የመጀመሪያው የሽልማት መርሃ ግብርም በመጪው ዓመት የሚከናወ ይሆናል።

ከዚያ በኋላም በዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሰው ልጆች ሰላም ፍቅርና በጎ ነገር ያበረከቱ አንድ ሴትና ወንድ እየተወዳደሩ ሽልማቱ በዓመቱ የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል።

ሽልማቱን የሚያገኙት አሸናፊዎች ሴቷ እቴጌ ጣይቱ ስም ወንዱ ደግሞ በአጼ ሚኒሊክ ስም የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም