አክሱም ለሚጓዙ የኮረና ቫይረስ ምርመራና ክትትል እየተደረገ ነው

55

አክሱም፤ መጋቢት 12 /2012 (ኢዜአ) የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎች የኮረና ቫይረስን ለመከላከል፣ ለራሳቸውና ለህብረተሰቡ ደህንነት ሲባል  የጤና ምርመራና ክትትል እያደረገ መሆኑን የአክሱም ከተማ ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።


የጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ሚሊዮን ኪዳነ ማሪያም ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የከተማውን ጥንታዊ ቅርሶች ለመጎብኘት የሚመጡ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ አገር ጎብኚዎች መኖራቸውን ተከትሎ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ልዩ ክትትልና ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ለዚህም ዝግጅትበከተማው  ከንቲባ የሚመራ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ  እንቅስቃሴ መጀመሩን አስረድተዋል።

የቅድመ መከላከልና የክትትል ሥራው በአክሱም አጼ ዮሀንስ አየር መንገድ፣  በሆቴሎችና  በቱሪስት መዳረሻ  ሥፍራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየተካሄደ መሆኑን  ኃላፊው ገልጸዋል።

በነዚህ ሥፍራዎች ላይ ለሥራና ለጉብኝት በሚመጡ ሰዎች ላይ ግብረ ሀይሉ እለታዊ ክትትል ማድረግ መጀመሩን ገልጸዋል።

ኃላፊውሆቴሎች በሽታው ለመከላከል የሚረዱ የንጽህና መጠበቂያ ግብአቶችን እንዲያሟሉ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

የአትራኖስ አለም አቀፍ ሆቴል ባለቤት አቶ ሰለሞን ተክላይ በሆቴላቸው በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ አገር ጎብኚዎች እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በመሆኑም የንጽህና መጠበቂያ እና በሽታውን ለመከላከል የሚያግዙ ግብአቶች ከሟሟላት  ጀምሮ ደንበኞች እና የሆቴሉ ሠራተኞች ቫይረሱን ለመከላከል ማከናወን የሚገባቸው እርምጃዎች ሁሉ እየተወሰዱ መሆኑን  አቶ ሰሎሞን ገልጸዋል።

በአየር መንገድ በኩል ወደ አክሱም የሚገቡና የሚወጡ ሁሉም መንገደኞች በጤና ባለሙያዎች የታገዘ የሙቀት መለካትሥራ እይተከናወነ  መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የአክሱም አፄ ዮሃንስ አየር መንገድ  ሥ ራ አስኪያጅ አቶ አረጋይ ገብረሚካኤል ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም