በአፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች የስፖርት ውድድር ላይ የሚሳተፉ 18 የአፍሪካ ሀገራት መቀሌ ገቡ

መቀሌ ሰኔ 23/2010ዘጠነኛው የአፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች የስፖርት ውድድር ላይ የሚሳተፉ  18 የአፍሪካ ሀገራት ተጠቃለው መቀሌ ከተማ ገቡ፡፡ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ አዘጋጅነት ከነገ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በሚቆየው የስፖርት ውድድር ላይ ለመሳተፍ ዛሬና ትናንት የገቡት ሀገራት ዩኒቨርስቲዎች ብዛት 56 ናቸው፡፡ የአፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች  ስፖርት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ዶክተር ማሉምቤት ራሌዝ  የውድድሩ ተሳታፊዎች ተጠቃለው መቀሌ መግባታቸው አስመልክተው ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንደገለጹት አፍሪካዊያን ወደ ሁለተኛ ቤታቸው ኢትዮጵያ መምጣታቸው ያላቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዲጠናክር ያግዛል። በውድድሩ ከ18 የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ የ56 ዩኒቨርስቲዎች ተሳትፊዎች ተጠቃለው መግባታቸው አረጋግጠዋል። ከ500 በላይ ተወዳዳሪዎች በአስር የስፖርት ዓይነቶች ውድድራቸውን እንደሚያካሄዱ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም