አትሌቶች ለኮሮና ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ ሆቴል ገብተው በጋራ ልምምድ ቢሰሩ የተሻለ ነው-- አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ

94

ኦሎምፒክ ቡድኑ የተመረጡ አትሌቶች የኮሮና ቫይረሱ ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ ሆቴል ገብተው ልምምዳቸውን በጋራ ቢሰሩ የተሻለ መሆኑን አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ ገለጸ።

የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በመጪው ክረምት በቶኪዮ የሚካሄደውን የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ውድድር እንደማይሰርዝ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አሊምፒክ ኮሚቴም የቶኪዮ ኦሎምፒክ የአትሌቶችን ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ላይ የተገኘው ሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ የቶኪዮ ኦሎምፒክ እንደሌሎች ውድድሮች ይራዘማል የሚል እምነት የለኝም ብሏል።

በምክንያትነት ያስቀመጠውም የኦሎሊምክ ውድድር የዓለም ሀገራት ችግር ውሰጥ በገቡበት ወቅት እንድነታቸውን ለማጠናከር የሚያግዝ በመሆኑ ነው ብሏል።

ኦሎምፒከን ለማዘጋጀት ብዙ ቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚደረግበት መሆኑ ሌላው ውድድሩ የማይራዘምበት ወይም የማይሰረዝበት ምክንያት መሆኑን አብራርቷል።

በመሆኑም ለዚህ ውድድር የተመረጡ አትሌቶችም ውድድሩ ላይካሄድ ይችላል በሚል መዘናጋት እንደማይግባቸው ነው አትሌት ሃይሌ የተናገረው።

ለዚህም የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ብሄራዊ ቡድን ከወዲሁ ዝግጀቱን በአግባቡና በሙሉ ስነልቦና መጀመር እንዳለበት ሃይሌ ምክሩን ለግሷል።

የብሄራዊ ቡድኑ አትሌቶች በወቅታዊነት የተከሰተው የኮሮኖ ቫይረስ ስጋት ምክንያት በግል ከመስራት ይልቅ በቡድን ሆቴል ተሰባስበው ቢሰሩ አስፈላጊው ጥቃቄ ስለሚደረግላቸው ተጋላጫነታቸው ይቀንሳልም ብሏል።

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የቶኪዮ አሊምፒክ የህክምና ኮሚቴ አባል ዶክተር ቃል ኪዳን ዘገየ በመላ ሀገሪቱ በርካታ ስፖርተኞች የሚካፈሉበት ውድድርና ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ቢከለከልም ለኦሊምፒክ ቡድኑ የተለየ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ገልጸዋል።

ከተደረጉት ቅድመ ዝግጀቶች መካከል ስፖርተኞች የሚያርፉበት ሆቴልን ፀረ ተዋሲያን ከመርጨት ጀምሮ ስፖርተኞች የሚመገቡበት ክፍልና የሚጠቀሙበት ሊፍትም ለሌሎች ተጠቃሚዎች የተከለከለ ይሆናል።

አትሌቶችን የሚያስተናገዱ የሆቴሉ ሰራተኞችም ጭምር የተለየ ክትትል እንደሚደረግባቸው ነው የተገለጹት።

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር ባደረጉት የቪዲዮ ኮንፈረስ ውድድሩ በምንም አይነት መልኩ እንደማይሰረዝ አረጋግጠዋል።

የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የየሀገራቱን የኮሮና ስርጭ ሁኔታ ለመከታተል የሚያችስል አሰራር ዘርገቶ ከየሀገራቱ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አባል ሀገራት ጋር የሚገናኝበትን ሁኔታ እያማቸቸ  መሆኑንም ጠቁመዋል።

በዚህም መረጃዎች በመለዋወጥ ውድድሩን ሃላፊነት በተሞላበት መልኩ ለማዘጋጀት እንደተዘጋጁ ተገልጿል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም