በኤዢያ በስፋት የሚካሄደው የደን ጭፍጨፋና ፈጣን የከተሞች መስፋፋት ለገዳይ ቫይረሶች መነሻ ነው…ባለሙያዎች

752

መጋቢት 2/2012 (ኢዜአ) በኤዢያ ሀገራት እየጨመረ በመጣው የደን ጭፍጨፋና የከተሞች ማስፋፋት እንዲሁም የመንገዶች ግንባታ ኮሮናን ጨምሮ ተላላፊ ለሆኑ ቫይረሶች መስፋፋት መንስኤ ነው ሲሉ የጤና እና የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች ገለጹ ፡፡

በአሁኑ ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃ ከ119ሺ በላይ ሰዎች ለተጠቁበት እና ከ4ሺ 200 በላይ ሰዎች ለሞቱበት ኮሮና መነሻው ከዱር እንሰሳት የመጣ ቫይረስ መሆኑን ነው ባለሙያዎቹ የሚያስረዱት፡፡

እንደዚህ አይንት በሽታዎች እንደ ዱር ድመት ካሉ እንሰሳት የሚመጡ መሆናቸውን ገልጸው የኢቦላ ቫይረስ መነሻው የወፍ ጉንፋን መሆኑን በማስታወስ፡፡

ከእንሰሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ የመጡ ሲሆን የዚህ ምክንያት ደግሞ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ደኖች እየወደሙ በመምጣታቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሰዎች ከተፈጥሮ ጋር በስነ ህይወት ያላቸውን ትስስር በደንብ ሊያጤኑት ይገባል የሚሉት ባለሙያዎቹ ወደፊት ከባድ ሁኔታቸውን ሊያስከትል እንደሚችል አስታውቀዋል፡፡

የህዝቦች ቁጠር መጨመርን ተከትሎ በመሬት ላይ የሚደረገው ወረራ፣የደን ምንጠራ፣ የከተሜነት መስፋፋት፣ የተፈጥሮ  ሃብት ፍለጋዎች መጨመር ሰዎች ወደ እንሰሳት መኖሪያዎች የሚያደርጉትን ፍልሰት ከፍ አድርጎታል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ሰዎች ከእንሰሳት ጋር ባለቸው መቀራረብ ምክንያት ለተለያዩ ቫይረሶች  የመጋለጥ እድላቸው ሰፍቷል፡፡

60 በመቶ የሚሆነው ተላላፊ በሽታ ከእንስሳት የሚመጣ ሲሆን ፣ከጠቅላላው 75 በመቶው የሚከሰተው ደግሞ ሰዎች ለእርሻ ስራና ለልማት ብለው በሚያደርጉት የደን ምንጠራ ምክንያት ነው፡፡

በተለይም የኤዢያ አገራት  ለከተሞች ማስፋፋፊያነት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ላይ ከእንስሳት የሚመጡ በሽታዎችን ለመከላከል የቅድመ ዝግጅት  ስራዎችን በመስራት ረገድ ከፍተኛ ክፍተት እንደሚታይባቸው ተነግሯል፡፡

እ.ኤ.አ በ2018 ብቻ 12 ሚሊዮን ሄክታር ገደማ የሚገመት ዛፍ በእሳት ፣ በደን ምንጠራ እና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ወድሟል፣ ብራዚል፣ ኢንዶኖዢያ እንዲሁም ማሌዢያ በብዛት የዛፎች ውድመት ከተከሰተባቸው ቦታዎች ውስጥ መሆናቸውን ግሎባል ፎረስት ዎችን ዋቢ አድርጎ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡