ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጋር ተወያዩ

906

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30/2012 ዓ.ም ( ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጋር ዛሬ ጠዋት ተገናኝተው በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ መክረዋል።

በሠራዊቱ ዘንድ የሚከናወኑ ተቋማዊ እና መዋቅራዊ ለውጦችን በተመለከተም ምዘና አድርገዋል።