ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለመንግስት የስራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጡ

612

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24/2012(ኢዜአ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ዛሬ ለ15 የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል።

በዚሁ መሰረት አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ፣ ወይዘሮ ያለም ፀጋዬ፣ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ፣ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ፣ አቶ ባጫ ጊና፣ አቶ ይበልጣል አዕምሮ፣ አቶ ምህረተአብ ሙሉጌታ፣ አቶ ነብያት ጌታቸው እና አቶ ተፈሪ መለስን ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው ተሾመዋል።

አቶ አድጐ አምሳያ፣ አቶ ጀማል በከር፣ አቶ አብዱ ያሲን፣ አቶ ለገሠ ገረመው፣ ወይዘሮ እየሩሳሌም አምደማርያም እና አቶ ሽብሩ ማሞ ደግሞ በአምባሳደርነት ማዕረግ መሾማቸውን የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።