አዲሱ የፍጥነት መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂ በተሽከርካሪ ፍጥነት ምክንያት የሚደርሰውን አደጋ ይቀንሳል

117

የካቲት 22/2012 (ኢዜአ) አዲሱ የፍጥነት መቆጣጠሪያ መሣሪያ በተሽከርካሪዎች ላይ መገጠሙ በፍጥነት ምክንያት የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ  ጠቀሜታ እንዳለው ተገለጸ፡፡

የፍጥንት መቆጣጠሪያውን ቴክኖሎጂውን ከጂ.ፒ.ኤስ  ጋር በማጣመር ተፈጻሚነቱ ላይ ቁጥጥር ማድር እንደሚያስፈልግም ተጠቁሟል፡፡

መንግስት በአገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እጨመረ የመጣውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ የተለያዩ የመፍትሄ እርምጃዎችን ሲወስድና መመሪያዎችን ሲያጸድቅ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በተከሽርካሪዎች ፍጥነት ምክንያት የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ የፍጥነት መቆጣጠሪያ  መሳሪያን በሁሉም መኪኖች ላይ እንዲገጠም ባለፈው አመት ነው መመሪያ የጣው፡፡

በፒፖ የተባለ የመኪና ፍጥነት መቆጣጠሪያ አስመጪ ድርጅት የፍጥንት ቁጥጥር አስተዳር ሃላፊ አቶ ሙሉቀን ንጉሴ ለኢዜአ እንደገለጹት የፍጥንት መቆጣጠሪያ መሳሪያው በስራ ላይ በደንብ እየዋለ ሲመጣ፣ አንድ ተሽከርካሪ ከተፈቀደለት ፍጥንት በላይ እንዳይሄድ በማድረግ አደጋን ይቀንሳል፡፡

የተገጠመውን የፍጥነት መከታተያ የማይጠቀሙትን ወይንም ከተገጠመ በኋላ አልግሎት እንዳይሰጥ  የሚያደርጉትን አልያም ከተፈቀደላቸው የፍጥነት መጠን በላይ የሚያሽከረከሩ አሽከርካሪዎች ደግሞ የጂፒኤስ አቅጣጫ መከታተያ አብሮ በመግጠም መቆጣጠር ያስችላል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የፍጥንት መቆጣጠሪያ መሳሪያው አደጋን ከመቀነስ ጥቅሙ በተጨማሪ በመንገዶች የትራፊክ ፍስት ላይ በሚሰጠው መጃ መሰት የመንገድ ፖሊሲ ጥናቶችን ለመስራት ያግዛል ያሉት አቶ ሙሉቀን፤ የተሽከርካሪዎችን ፍጥነት በመገደብ  ወደ አየር የሚለቀቀውን የጭስ መጠን በመቀነስ ጤናማ አካባቢን ለመፍጠር ይረዳል ብለዋል ፡፡

በዘርፉ ላይ ከሰባት አመታት በላይ አገልግሎት በመስጠትና የፍጥነት መቆጣጠሪያውን የመግጠም ሰራ የሚሰራው የካሳ ሶፍት ዌር ትራኪንግ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ካሳ በበኩላቸው የፍጥንት መቆጣጠሪያው አንድን ተሽከርካሪ ከተፈቀደለት ፍጥነት በላይ እንዳይሄድ በማድረግ አደጋን ለመቀነስ ጉልኽ ጠቀሜታ ቢኖረውም መቆጣጠሪያው ቢበላሽ ወይንም እንዳይሰራ ቢደረግ መኪኖቹ የት እና በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ለማወቅ አይቻልም ብለዋል፡፡

ስለዚህ የአቅጣጫ መከታተያ ጂፒየሱን ከፍጥንት መቆጣጠሪያው ጋር አብሮ እንዲተገበር በመኪኖች ላይ የመግጠም ስራ የሚሰሩ ድርጅቶች በማገዝ የአቅጣጫ መከታተያው መገጠም አለመገጠሙንና የፍጥንት መቆጣጠሪያው እየሰጠ ያለውን አገልግሎት  መከታተል  እንደሚገባ ተናግረዋል ፡፡

መንግስት የፍጥነት መቆጣጠሪያውን ከሚገጠምልት የአቅጣጫ መከታተያ ጂፒኤስ ጋር ተጣምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ቢያደርግ የቁጥጥር ስራ ለመስራት ያመቸዋል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በአገሪቱ ባሉ ሁሉም ክልሎችና  የከተማ መስተዳድሮች ለሚገኙ ድርጅቶች የመግጠም ስራ እንዲሰራ በማድረግ ላይ  እንደሚገኝና ከዚሁ ጎን ለጎን የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ የገለጹት ደሞ የትራንስፖርት ባለስልጣን የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ይግዛው ዳኘው ናቸው፡፡

እንደ አቶ ይግዛው ገለጻ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በቀጣይ ከመንገድ ደህነንት ባለሙያዎች ጋር በመሆን የቁጥጥር ስራዎችን በጋራ ይሰራል፡፡

እስካሁንም  ከ3 ሺህ 6 መቶ በላይ ተሽከርካሪዎች ላይ የፍጥነት መቆጣጠሪያው ቴክኖሎጂው   እንዲገጠም መደረጉን ነው አቶ ይግዛው የጠቀሱት፡፡

ህዝብ በብዛት ለትራንስፖርት በሚጠቀምባቸው መነኻሪያዎች ደግሞ የፍጥንት መቆጣጠሪያውን በአገር አቋራጭ መኪኖች ላይ ለማስገጠም  ድርጅቶቹን  የማወዳደርና ውል የመፈጸም ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ 

በአሁኑ ወቅት የፍጥንት መቆጣጠሪያ መሳሪያውን ለመግጠም 27 ድርጅቶች ወደ ስራ የገቡ ሲሆን መሳሪያውን ለመግጠም ከ11ሺ አስከ 12ሺ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም