በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ስራውን ጀመረ

400

መቀሌ ኢዜአ የካቲት 20/2012 ዓ/ም በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራውን በይፋ መጀመሩን አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሰሎሞን ገብረአረጋዊ ለኢዜአ እንደገለፁት ቅርንጫፉ ከሚያስፈልጉት  26 ሰራተኞች መካከል የግማሽ ሰራተኞችን ቅጥር  አካሄዷል።

የቀሩ የህግ ባለሙያዎች የሚገኙባቸው ባለሙያዎች ቅጥር በቅርብ ቀናት ለማከናወን እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

ከዚህ በተጓዳኝም ለስራው መሳካት የሚያስፈልጉት የተለያዩ የቢሮ ቁሳቁሶች እያሟላ መሆኑን አስረድተዋል።

በትግራይ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል በምርጫ ቦርዱ መመሪያ መሰረት እስከ አሁን እውቅና የተሰጣቸው ሦስት ድርጅቶች ብቻ ናቸው ብለዋል።

እውቅና የተሰጣቸው የፖለቲካ ድርጅቶችም  ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ/ህወሐት/፤ብሄራዊ ባይቶና ዓባይ ትግራይ እና ሳልሳይ ወያነ መሆናቸውን የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አስታውቀዋል።