ልማት ባንክ የአገር በቀል ምጣኔ ሃብት ማሻሻያውን ይደግፋል የተባለ ስትራቴጂ ይፋ አደረገ

95

አዲስ አበባ፣ የካቲት19/2012 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የአገር በቀል ምጣኔ ሃብት ማሻሻያውን ይደግፋል ያለውን ስትራቴጂክ ዕቅድ መተግበር ጀምሬያለሁ አለ።

ባንኩ የዕቅድ ትግበራውንና ያለፉት ስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙን አስመልክቶ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም፣ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅዱ ኢትዮጵያ እየተገበረችው ያለውን የአገር በቀል ምጣኔ ሀብት ማሻሻያ በሚደግፍና አብሮ በሚሄድ መልኩ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።

የባንኩን የቢዝነስ ሞዴልና የፋይናንስ ምጣኔ ማጥናትና ከአገር በቀል ልማት ዕቅድ ጋር ማጣጣም፣ አሰራሩን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማደራጀት፣ በባንኩ የሚታየውን የተከማቸ ወይም አጠራጣሪ ብድር መቀነስና አዲስ እንዳይገባ መጠንቀቅ፣ ለባለሃብቱ ብድር ማቅረብና ሌሎችም የሪፎርሙ ዋና ዋና ትኩረቶች ናቸው ተብሏል።

በተጨማሪም ከብድር አሰጣጥ ጋር በተገናኘ ተጠያቂነትን ማስፈን የስትራቴጂክ ዕቅዱን እንደሚያግዝ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ኃይለእየሱስ በቀለ ተናግረዋል።

የባንኩ አጠቃላይ ሃብት ከ89 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱም ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም