በትግራይ የሴቶች ብስክሌት ውድድር ተጀመረ

81

የካቲት 19/2012 (ኢዜአ) የክልሉ ማጣሪያ ውድድር ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ነው።

ከመቀሌ ወደ ዓብይ ዓዲ ከተማ በሚወስደው መንገድ 24 ሴት ብስክሌተኞችን ከጥዋት ጀምሮ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን ውድድር  እያካሄዱ ነው።

ነገ ደግሞ በዚሁ መስመር ሴት ብስክሌተኞቹ 80 ኪሎ ሜትር በሚሸፍን ርቀት ላይ ፍክክራቸውን ያካሄዳሉ።

በመጪው እሁድ በመቀሌ ከተማ በሚኖረው የማጠቃለያ ውድድርም 60 ኪሎሜትር የሚሸፍን ርቀት ላይ ይወዳደራሉ።

በውድድሩ የትራንስ ኢትዮጵያ፣ የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ፣ መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጅነሪንግ እና የመቀሌ 70 እንደርታ ክለቦችን ወክለው የቀረቡ ተወዳዳሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

 በአጠቃላይ ውጤት አንደኛ  የወጣች ክልሉን ወክላ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የማጣሪያ ውድድር እንደምትሳተፍና ሁለተኛው  ደግሞ  በተጠባባቂነት እንደምትወከል በክልሉ ብስክሌት ፌዴረሽን የውድድርና ፌስቲቫል ከፍተኛ ባለሙያ መምህር ፀሐየ አደም ለኢዜአ ገልጸዋል።