በአሰላ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው

96

አዳማ፤ የካቲት 19/2012(ኢዜአ) የአሰላ ከተማ ነዋሪዎች በሀገሪቱ እየመጣ ያለውን ለውጥና የብልፅግና ጉዞን በመደገፍ ዛሬ በአሰላ አረንጓዴ ስታዲዮም ሰልፍ በማካሔድ ላይ ይገኛሉ ።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ ከአሰላ ከተማ ነዋሪዎች በተጨማሪ በአርሲ ዞን ከሚገኙ 25 ወረዳዎች የመጡ በርካታ የህብተተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

ሰልፈኞቹ ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ብልፅግናን የሚደግፉ የተለያዩ መፈክሮች በማሰማት ወደ አሰላ አረንጓዴ ስታዲዮም በማምራት ላይ ናቸው ።

ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በዘላቂነት እናቆየዋለን ! በመደመር እሳቤ ወደ ብልፅግና የሚደረገውን ጉዞ እናሳካለን ! አንድነታችንን በማጠናከር ከብልፅግና ፓርቲ ጎን እንቆማለን ! የሚሉና ሌሎች በርካታ መፈክሮችን ሰልፈኞቹ በማስተጋባት ላይ ናቸው ።

በሰልፉ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ሲሆኑ የኦሮሚያ ክልል ፣ የአርሲ ዞንና የአሰላ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።