የአንበጣ መንጋን ለመከላከል ተጨማሪ ገንዘብ ተጠየቀ

128

የካቲት 18/2012 በአፍሪካ እና ኤስያ የተከሰተውን አንበጣ መንጋን ለመቆጣጠር ፋኦ ተጨማሪ ገንዘብን   ጠየቀ ፡፡

የተባበሩት የእርሻና የምግብ ድርጅት እንዳስታወቀው አንበጣ መንጋው በዚሁ ከቀጠለ የምስራቅ አፍሪካን ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ እንደሚከት ሲገልጽ ችግሩን ለመቆጣጠርም ተጨማሪ 62 ሚሊዮን ዳላር ከረጅ ድርጅት እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡

በቅርብ ጊዜ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የተከሰተው   የአንበጣ መንጋ ወደ ኩዌት ፣ባህሬን፣ኳታር እና ኢራን የባህር ዳርቻዎች ተስፋፍቷል፡፡

አንበጣው በኬንያ፣ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በከፍተኛ ደረጃ በመስፋፋቱ ቢያንስ 100,000 ሄክታር ሰብልን ሲጎዳ ችግሩን ለመቅረፍም   ፀረ-ተባይ መድሀኒት መጠቀም አስገዳጅ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

ፋኦ ባለፈው ጥር የአንበጣውን  መንጋ ለመቆጣጠር  ከረጂዎች  እፈልጋለሁ ያለው  76 ሚሊዮን ዶላር አሁን  ወደ 138 ሚሊዮን ዶላር ቢያሸቅብም ከዚህም ውስጥ እስካሁን 33 ሚሊየን ዶላር  ብቻ  ነው የተገኘው፡፡

የምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣ  መቆጣጠሪያ ማስተባሪያ  ድርጅት ኃላፊ እስጢፋኖስ ነጃክ እንዳሉት “የአውሮፕላን እና ፀረ-ተባይ እጥረት ለስራችን ፈተና ሆኗል” ፡፡

አንበጣውን ለማጥፋት ኢትዮጵያ አምስት በኬንያም ከሚያስፈልገው 20 አውሮፕላን ስድስት ብቻ መመደባቸው የችግሩን አስከፊ አድርጎታል በማለት ፡፡ምንጭ በቢሲ