የኢትዮጵያ ዜጋ ተኮር እርምጃ ውጤታማ ነው

132
የካቲት 18/2012(ኢዜአ) በኢትዮዽያ የተደረገው ለውጥ ዜጎች ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ እያደረገ መሆኑን የኬንያው ዘኢስት አፍሪካን  ድረገጽ አስነበበ።

ባለፈው ሳምንት በኬንያ ጥገኝነት ተሰጥቷቸው የኖሩ 76 እንዲሁም በታንዛንያ የቆዩ 128 ኢትዮዽያውያን ዜጎችን ማእከል ባደረገው የዲፕሎማሲ ጥረት ወደ ኢትዮዽያ እንደተመለሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃልአቀባየ አቶ ነቢያት ጌታቸው ገልጸዋል።

ባለፈው አንድ አመት ታንዛንያና ኬንያን ጨምሮ ከ10 በላይ ሃገራት ውስጥ ሲኖሩ የነበሩ ከ120 ሺህ በላይ ኢትዮያውያን ወደ ሃገራቸው እንደተመለሱ ያነሱት ቃል አቀባዩ በኬንያ የተጠለሉ ከ28 ሺህ በላይ ስደተኞች እና ወደ ደቡብ አፍሪካ በህገወጥ መንገድ ሲሄዱ ተይዘው በታንዛንያ እስር ቤቶች የሚማቅቁ 1500 ስደተኞችን ለመመለስ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

በኬንያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ቃልአቀባይ ዩጂን ባዩን ለድረገጹ እንደተናገሩት ኢትዮዽያና ኬንያ ስደተኞቹን መልሶ ለማቋቋም ምቹ ሁኔታ ስለመኖሩ ተስማምተዋል።

የመጀመሪያው የተመላሾች በቡድን ካኩማ ከተባለው የስደተኞች መጠለያ ወደ ድሬዳዋ በረራዎችን ያገረገ እና ስደተኞቹ ወደ ጅግጅጋ የሚዛወሩ መሆኑን የተናገሩት ቃልአቀባይዋ ከዳዳብና ካኩማ መጠለያዎችም ከ4ሺህ በላይ ኢትዮዽያውያን በኮሚሽኑ ድጋፍ ወደ ሃገራቸው እንደሚሸኙ  አሳውቀዋል፡፡

ስደተኞቹ እያደገች ካለችው ሃገራቸው ጋር አብረው እንዲለወጡና እድሜ ልካቸውን ስደተኛ መሆን እንደሌለባቸው መስሪያ ቤታቸው በውጭ የሚገኙ ኢትዮዽያውያንን ጥቅሞችና መብቶች ለማሰከበር እየሰራ መሆኑን  አቶ ነቢያት አብራርተዋል።





የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም