አልጄሪያ ከአፍሪካ ሁለተኛዋ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃች ሀገር ሆናለች

63

የካቲት 17/2012 ከቻይና ተነስቶ በበርካታ ሀገራት በመዛመት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን  ህይወት እየቀጠፈ የሚገኘው ኮሮና  አልጄሪያ መግባቱን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስተር አስታውቋል፡፡

በቅርቡ  አልጄሪያ በገባ አንድ ጣልያናዊ  መዛመቱ የተነገረው ቫይረሱ አልጄሪያም  ከግብፅ ቀጥሎ ሁለተኛዋ በቫረሱ የተጠቃች  ሀገር ሆናለች፡፡

ይህንንም ተከትሎ ፕሬዚዳንት አብድልማዳጅ ተቤባን ሁሉም የህክምና ባለሞያዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በቲውተር ገፃቸው ላይ አስታውቀዋል፡፡

ይህም በፖለቲካዊ ሆኔታዋ ቀውስ ላይ ላለቸው አልጄሪያ አስቸጋሪ እንደሚሆንባት ተነገሯል፡፡

በጣሊያን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሶስት መቶ የደረሰ ሲሆን 11 ሰዎች በቫይረሱ ሞተዋል ሲል ያስነበበው ቢቢሲ ነው፡፡