ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ እንደማትሳተፍ አስታወቀች

510

አዲስ አበባ፤ የካቲት 18/2012 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ከሱዳን እና ግብጽ ጋር በአሜሪካ በሚካሄደው የሶስትዮሽ ድርድር ላይ እንደማትሳተፍ ገልጻለች፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ በኢትዮጵያ፣ በግብጽ እና በሱዳን መካከል በአሜሪካ ግምጃ ቤት ጸሃፊ እና የአለም ባንክ ፕሬዚደንት በታዛቢነት በሚሳተፉበት የሶስትዮሽ ድርድር በአሜሪካ ሲካሂድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

የሶሽትዮሽ ድርድሩ ቀጥሎ ከነገ ሃሙስ እስከ አርብ ድረስ ለሁለት ቀናት በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ሊካሄድ የታሰበው የውይይት መድረክ ላይ ኢትዮጵያ እንደማትሳተፍ የውሃ ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን በአገር ውስጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገውን ውይይት ባለማጠናቀቁ ምክንያት ነው ኢትዮጵያ በመድረኩ እንደማትሳተፍ ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

በተጠቀሰው ጊዜ በአሜሪካ በመገኘት ውይይቱን ማድረግ እንዳልተቻለ ጥሪውን ላደረገው የአሜሪካ ግምጃ ቤት ጽ/ቤት ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡