ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፕሬዚደንት ጂንፒንግ ጋር ተወያዩ

850

የካቲት 17/2012 (ኢዜአ) ከፕሬዚደንት ዢ ጂንፒንግ ጋር የኖቭል ኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ጨምሮ፣ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጸ።

በቻይና ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ልዩ እንክብካቤና ድጋፍ የሚያደርጉ መሆናቸውን ከፕሬዚደንት ጂንፒንግ በመስማቴ ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በዚህ አኳያ የቻይና መንግሥት በሚያከናውነው ሥራ  መደሰታቸውን የገለጹ    እስካሁንም ለኢትዮጵያውያን ስለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋዊ የፌስቢክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።