በምእራብ ሸዋ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው

70
አምቦ የካቲት 15/2012 (ኢዜአ) የምዕራብ ሸዋ ዞን ነዋሪዎች በሀገሪቱ የመጣውን ሁለንተናዊ የለውጥ ሂደት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አጋርነታቸውን ለመግለፅ ዛሬ  የድጋፍ ሠልፍ እያካሄዱ ነው። በአምቦ ከተማ እየተካሄደ ባለው የድጋፍ ሰልፍ  ከ22 ወረዳዎች የተውጣጡ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎችና በአምቦ ከተማና አካባቢው የሚኖሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ናቸው ። ከጠዋቱ 3 ሰዓት  ጀምሮ እየተካሔደ ባለው የድጋፍ ሰልፍ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚመራውን ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን እገዛ አንደሚያደርጉ ሰልፈኞቹ በያዙዋቸው መፈክሮች አስተጋብተዋል ። ነዋሪዎቹ የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት በሞተር ብስክሌቶችና በፈረሰኞች ታጅበው በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች በመዘዋወር ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያላቸውን ድጋፍ በመግለፅ ላይ ናቸው ።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም