ጅማ ዩኒቨርስቲ 3ሺህ 185 ተማሪዎችን አስመረቀ

140
ጅማ፣ የካቲት 14/2012 (ኢዜአ) ጅማ ዩኒቨርስቲ 3ሺህ 185 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል። የጅማ የኒቨርስቲ ፕሬዘዳንት ዶክተር ጀማል አባ ፊጣ በምረቃው ስነ ስርዓቱ ወቅት እንደተናገሩት "ዛሬ ከጅማ ዩኒቨርስቲ ተመራቂዎች ሀገራችሁ  ከእናንተ ከምንግዜውም በላይ እንድታገለግሏት ትፍልጋለች "ብለዋል፡፡ ዩኒቨርስቲው ያስመረቀው ከስድስት ኮሌጆች፣ ሁለት ኢንስቲትዩቶች እና ድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት በተለያዩ ሙያዎች ስልጠናቸው ነው፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል  834 ሴቶች እንዲሁም 11  የሱማሌ ላንድና የሩዋንዳ ዜጎች ይገኙበታል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ የአለም ሀገራት የተወጣጡ አንድ መቶ ስልሳ ስምንት  ሰዎችን  እያስተማረ እንደሚገኝም ተመልክቷል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም