ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ሰመራ ገቡ

4613

አዲስ አበባ  ሰኔ 21/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሰመራና አካባቢዋ ህዝብ ጋር ለመወያየት ዛሬ ማለዳ ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መዲና ሰመራ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰመራ ሲደርሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል ስዩም፣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ህብረተሰቡ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ከህብረተሰቡ ጋር ከሚያደርጉት ውይይት በተጨማሪ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በሰመራ ለሚገነባው የኢንዱስትሪ ፓርክ የመሰረተ ድንጋይ ያስቀምጣሉ።