የኮምፒውተር አጠቃቀምን ያቀለሉት የከት፣ኮፒና ፔስት ፈጠራዎች ባለቤት የሆነው ባለሙያ ህይወቱ አለፈ

75
ኢዜአ የካቲት 12/2012 የኮምፒውተር  አጠቃቀምን ያቀለሉት የከት፣ኮፒና ፔስት ፈጠራዎች ባለቤት የሆነው የኮምፒውተር ባለሙያ ህይወቱ ማለፉን ቢ ቢ ሲ ዘግቧል። መረጃዎችን በቀላሉ በኮምፒውተር ላይ ለመፈለግና ለመተካት የሚያስችሉና ሌሎች ፈጠራዎችም በባለሙያው መሰራታቸው በዘገባው ተመልክቷል። ይሀውም በኮምፒውተር የሚከናወኑ ስራዎችን በማቃለሉ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተጠቅሷል። የኮምፒውተር ባለሙያ የነበሩት ሚስተር ላሪ ቴስለር ህይወቱ በ74 አመታቸው  ማለፉቸውም ተገልጿል። ሚሰተር ላሪ እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ መጀመሪያ ላይ በዘርፉ ሞዴል ከሚባሉት መካከል የሚጠቀሱና ኮምፒውተሮች ለበርካታ ሰዎች ተደራሽ ባልሆኑበት ወቅት ላይ ስራ መጀመራቸውም ተጠቅሷል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም