ናይጄሪያ በነዳጅ ስርቆት ምክንያት 750 ሚሊዮን ዶላር አጥታለች

95
የካቲት 11/2012 (ኢዜአ) ናይጄሪያ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ዓመት 2019 በነዳጅ ስርቆት ምክንያት ለመንግስት ገቢ መሆን የነበረበትን 750 ሚሊዮን ዶላር ማጣቷን የሀገሪቱ ብሔራዊ ነዳጅ ኮርፖሬሽን አስታውቋል፡፡ የኮርፖሬሽኑ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ማላም ሜል ኪያሪ በሰጡት መግለጫ እያደገ የመጣውን የነዳጅ ስርቆት ባፋጣኝ ማቆም ካልተቻለ  በኮርፖሬሽኑ ስራ ላይ ትልቅ የደህንነት ስጋት እንደሚጥል ገልጸዋል፡፡ በተለይም በጊኒ በህረ ሰላጤ በኩል ያለው የጸጥታ ስጋት ከናይጄሪያ አልፎ ለዘርፉ የንግድ ሂደት ትልቅ አደጋ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የአገራቸው የኢኮኖሚ መሰረት በመሆኑም ጉዳዩ የብሄራዊ ደህንንት ስጋት ተደርጎ እንደሚቆጠር ተናግረዋል፡፡ በዘርፉ ላይ የሚታየው ችግር  ከነዳጅ ውንብድና እና ስርቆት አልፎ  መሰረተ ልማት ዝርፊያ እንደሚካሄድበትና ሰራተኞችም እንደሚታገቱበት ተገልጿል፡፡ እ.ኤ.አ በ2016 በአለም አቀፍ ደረጃ 62 የነዳጅ መርከበኞች የታገቱ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ሰላሳ አራቱ በጊኒ ባህረ ሰላጤ የነዳጅ ማስተላለፊ የተፈጸመ መሆኑን የናይጄሪያው ቫንጋርድ አስነብቧል፡፡ የነዳጅ ዘርፉ በናይጄሪያ እ.ኤ.አ 2019 65 በመቶውን የመንግስት ገቢ ያስገኛ ሲሆን ሀገሪቱ በጠቅላለው ወደ ውጪ ከላከችው አቅርቦቶች ደግሞ 88 በመቶውን እንደሸፈነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም