የአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ አዲስ አበባ ገቡ

67
የካቲት 9/2012 (ኢዜአ) የአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ  ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል። ፖምፒዮ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አቀባበል አድርገውላቸዋል። ማይክ ፖምፒዮ በነገው እለት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር የሁለቱን ሀገሮች የሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ። በተጨማሪም ከኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት  ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል። (ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም