በሊጉ ጨዋታ የነቀምቴ ከተማ የእግር ኳስ ክለብ ተጋጣሚዎች ተጋጣሚውን አሸነፈ

106

ነቀምቴ ኢዜአ የካቲት 09/2012 ፡- በአስረኛው ሣምንት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የእግር ኳስ ጨዋታ የነቀምቴ ከተማ የእግር ኳስ ክለብ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ክለብን ሁለት ለአንድ አሸነፈ ፡፡

የነቀምቴ  ክለብ አሸናፊ የሆነባቸው ግቦች ያስቆጠረው ትላንት በሜዳው ተጋጣሚውን ባስተናገደበት ጨዋታ  በ20ኛውና  በ85ኛው ደቂቃ በኦብሳ በፍቃዱ አማካይነት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ክለብ ደግሞ  በ39ኛው ደቂቃ ላይ አቻ የሚያደርገውን ግብ ቢያስቆጥርም ከመሸነፍ አልዳነም፡፡

ሁለቱ ክለቦች በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ አንዳንድ ግብ ቢያስቆጥሩም ከጨዋታ ውጭ ነው በሚል በዳኛው ተሽሮባቸዋል ፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ክለብ አሰልጣኝ አቶ በፀሎት ልዑልሰገድ  በሰጡት አስተያየት አቻ የምታደርጋቸውን ግብ ቢያስቆጥሩም ከጨዋታ ውጭ ነው በማለት በዕለቱ ዳኛ መሻሩ አግባብ እንዳልሆነ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡