ፌስቡክ  በአፍሪካ   የኢንተርኔት ደህንነት ዙሪያ ሊሰራ ነው

176

የካቲት 3/2012 (ኢዜአ)  ፌስቡክ ከዘጠኝ አጋር አካላት ጋር በመተባበር  ለአፍሪካ  የኢንተርኔት  መረጃ ደህንነት  እሰራለሁ አለ ፡፡

ፌስቡክ ከሰሃራ በርሃ በታች ላሉ  አፍሪካ አገራት የኢንተርኔት መረጃ  አጠቃቀምንና አገልግሎቱን ለማሳደግ ከዘጠኝ መንግስታዊ ና  መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር  እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

ፌስቡክ ይህን ያለው ደህንነቱ የተጠበቀ ኢንተርኔት ቀንን በማስመልከት የግንዛቤ ማስጨበጫ  ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

የአገራቱ  የፌስቡክ የስትራቴጂክ ሚዲያ አጋርነት ኃለፊ ጆሴሊን ሙሁቱ ሬሚ በዚህ ወቅት እንዳሉት ለፌስቡክ እና ኢኒስታግራም  ተጠቃሚዎች በተለይም ለወጣቶች፣ በበቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው  ከአጋር አካላት ጋር አንሰራለን  ብለዋል፡፡

በቅርቡ በኢኒስታግራም ላይ አላስፈላጊ ሀሳቦችን፣ አስተያቶችን ፣መልክቶችንና ምስሎችን የሚለይ አዲስ  አሰራር  መተግበሩንም  ተናግረዋል፡፡

በተለይም በአሁኑ ወቅት  አርተፊሻል ኢንተለጀንስ በመጠቀም ፌስቡክና ኢኒስታግራም በቀጥታ የሚተላለፉ የዘረኝነትና የወንጀል ወይንም የግድያ አሳቦችን በመቆጣጠር ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡