አፍሪካ ታዳሽ ኃይሏን ለመጠቀም የግሉን ዘርፍ ማሳደግ ይገባታል

73
የካቲት 3/2012 (ኢዜአ) አፍሪካ ያላትን ታዳሽ ኃይል ለመጠቀም የግሉን ዘርፍ ማሳደግ ይገባታል ተባለ። በአፍሪካ ታዳሽ ኃይል አቅርቦትና አጠቃቀም ላይ ያተኮረ የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄ ነው። የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከአጋር አካላት ጋር ባዘጋጀው በዚህ ፎረም የዚምባብዌና የሞዛምቢክ አገራት መሪዎችን ጨምሮ የአገራቱ ተወካዮችና የተለያዩ ዓለም አቀፍ የግል ድርጅቶች ተዋናዮች ተሳትፈውበታል። በፎረሙ አፍሪካ በፀሀይ፣ በውሃና በጂኦ ተርማል ታዳሽ ኃይል ላይ ያላትን እምቅ አቅም ማሳደግ የሚቻልባቸው ጉዳዮችና ተግዳሮቶችም ተነስተዋል። የኃይል ዘርፉ ለሁሉም አገራት ምጣኔ ሀብታዊ ዘርፎች የተሳሰረ፣ የአህጉሪቷን ወጣቶች ስራ የሚፈጥር ቢሆንም በፋይናንስ፣ በመሰረተ ልማት አለመሟላትና ሌሎች ተግዳሮቾች ሳቢያ ውጤታማ አለመሆኑ ተነስቷል። የመንግስትና የግል ኢንቨስትመንት አጋርነትን ማሳደግ እንደ አማራጭ የተጠቀሰ ሲሆን ለዚህ ደግሞ መንግስታት የግሉ ዘርፍ እድገት ላይ አሉታዊ ጫና የሚያሳድሩ ፓሊሲዎችን መፈተሽ እንዳለባቸው ተጠቁሟል። አፍሪካ የታዳሽ ኃይል አቅሟ ከፍተኛ ቢሆንም እስካሁን ከ570 ሚሊዮን በላይ አፍሪካዊያን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ አለመሆናቸውን ጥናቶች ያመላክታሉ።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም