ቅዱስ ጊዮርጊስ ውልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን በማሸነፍ መሪነቱን ተረከበ

124

መቀሌ  የካቲት 1/2012 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረጉ አራት ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ውልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 4 ለ 1 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ከፋሲል ከነማ ተረክቧል፡፡

በትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲዮም በተካሔደው ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ አሸንፎ   መውጣት የቻለው  አቤል ያለውና ጌታነህ ከበደ ባስቆጠሯቸው ሁለት ሁለት ግቦች አማካኝነት ነው።

ለወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ዳዊት ወርቁ በ34ኛው ደቂቃ ላይ በፍፁም ቅጣት ምት  ክለቡን ከመሸነፍ ያላዳነችውን አንድ ጎል አግብቷል።

በዚህም ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥቡን ወደ 26 ከፍ በማድረግ የሊጉን መሪነት ከፋሲል ከነማ ተረክቧል፡፡

ወልዋሎ ደግሞ ባለው 12 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ሌሎች በተደረጉ ጨዋታዎች ሀዋሳ ከተማ  ጅማ አባጅፋርን 1ለ0 ፣በህርዳር ከተማ ሰበታ ከተማን 3ለ2 እንዲሁም ድሬደዋ ከስሁል ሽሬ አንድ አቻ ተለያተዋል ፡፡

ነገ በሚደረግ የሊጉ ቀሪ   ጨዋታ ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን  ሲያስተናግድ  ማክሰኞ ደግሞ ሀዲያ ሆሳዕና ከወላይታ ድቻ ይጫወታሉ ፡፡