በየመን የአልቃይዳ አሸባሪ ቡድን መሪ በአሜሪካ መከላከያ ሀይል በተደረገበት ጥቃት ተገደለ

101

ኢዜአ ጥር 29/2012 በየመን ‘ቃሲም አል ራይሚ’ የተሰኘ የአልቃይዳ መሪ  በአሜሪካ መከላከያ በድሮን በተፈጸመ ጥቃት መገደሉን አሜሪካ አስታወቀች።

‘ቃሲም አል ራይሚ’ እ.ኤ.አ ከ2015 ጀምሮ የጂሃዲስት ቡደን  መሪ የነበረ ሲሆን ከ2000 ጀምሮ ከተከሰቱ ጥቃቶች ጋርም ግንኙነት እንዳአለው የኋይት ሀውስ ቢሮ አስታውቋል።

የአል ራይሚ  ግድያ ባለፈው ወር መጨረሻ ላይ ጀምሮ ሲነገር ቢቆይም ኋይት ሀውስ  ቡድን መሪው መገደሉን አረጋግጧል።

ሆኖም ግድያው መቼ እንደተከናወነ በመግለጫው አልተጠቀሰም ።

የቡድኑ መሪው መገደል በየመንና በአለም አቀፍ ደረጃ የአል ቃይዳን እንቅስቃሴ ለማዳከም እንደሚያስችል ተጠቁሟል።

ለአሜሪካ ደህንነት ስጋቶች የሆኑ እንቅስቃሴዎችን ከማስወገድ አንጻርም ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።

ምንጭ ቢ ቢ ሲ