በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሟቾች ቁጥር ወደ 426 አሻቀበ

59
ጥር 26/2012 በቻይና በተከሰተው የኖቭል ኮሮና ቫይረስ  አንድ የውጭ ሀገር ዜጋን ጨምሮ የሟቾች ቁጥር  426 መድረሱ ተነገረ፡፡ ሌሎች 20 ሺህ 471 ሰዎች ደግሞ የበሽታው ምልክት እንደተገኘባቸው ተነግሯል፡፡ በሽታው እንዳለባቸው ከተረጋገጠ 20 ሺህ 471 ሰዎች መካከል 159 የሚሆኑት ደግሞ የሌላ ሀገር ዜጎች ናቸው፡፡ አስካሁን ድረስ በተደረገላቸው የህክምን እርዳታ 632 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ቢሆንም የጤና ባለሙያዎች ግን መልሶ እንዳያገረሽባቸው ያላቸውን ስጋት ገልፀዋል፡፡ በቻይና 31 ግዛቶች ፣ በራስ ገዝ ክልሎች እና ማዘጋጃ ቤቶች የደረጃ 1 የአደጋ ጊዜ ምላሽ መስጫ ማዕከሎች ተቋቁመው አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡ (ሲጂቲኤን)
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም