በ2020 እ.ኤ.አ የአፍሪካ ምጣኔ ሀብት 3.9 በመቶ ያድጋል

133

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 22/2012 የአፍሪካ ልማት ባንክ በኮትዲቯሯ ዋና ከተማ አቢጃን ይፋ ባደረገው ሪፖርት እ.ኤ.አ በ2020 የአፍሪካ ምጣኔ ሀብት 3.9 በመቶ ያድጋል ፡፡

በሳለፍነው 2019 የፈረንጆቹ ዓመት የ3.4 በመቶ እድገት የነበረው የአፍሪካ ምጣኔ ሃብት በ2020 የ3.9 እንዲሁም በ2021 እ.ኤ.አ በ4.1 በመቶ እንደሚያድግ ተንብይዋል፡፡

ይህም  ከዚህ ቀደም አፍሪካ ታሳካዋለች ተብሎ ከተተነበየው ምጣኔ ሀብት እድገት አንጻር ዝቅ ማለቱን ባንኩ አመልክቷል፡፡

በምክንያትም  አልጄሪያ፣ግብጽ፣ ሞሮኮ፣ ናጄሪያና ደቡብ አፍሪካ አገራት  እድገት  ከተገመተው አራት በመቶ ወደ 3.1 በመቶ መውረዱን በመጥቀስ፡፡

በ2019 እ.ኤ.አ የታየው የምጣኔ ሃብት እድገት በአስር አመት ውስጥ ያልታየ መሆኑን የገለጸው ሪፖርቱ በአህጉሪቱ እየጨመረ የመጣው ወደ ውጪ የሚላክ  ምርት ጉልህ ድርሻ ማበርከቱን አመልክቷል፡፡

ከአፍሪካ ወደ ውጪ የሚላኩት ምርቶች እድገት በዚሁ ከቀጠለ የአህጉሪቷን  ምርት  ከማሳደግ አልፎ ለወደፊቱ ከፍተኛ መሰረት እንደሚጥል የአፍሪካ ልማት ባንክ ተናግሯል፡፡

የዚሁ አመት የተናጠል  ውጤት ሲታይ የምስራቅ አፍሪካ አገራት 5 በመቶ የምጣኔ ሃብት ፈጣን እድገት በማሳየት ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ የሰሜን አፍሪካ አገራት በ4.1 በመቶ እድገት ሁለተኛ ደረጃን ፣ በሶስተኝነትም የምዕራብ አፍሪካ አገራት የ 3.7 በመቶ እድገት ማሳየታቸውን የናይጄሪያው ቫንጋርድ አስነብቧል፡፡