የድጋፍ ሰልፉን ተከትሎ ለተጎዱ ዜጎች አሁንም ደም የመለገስ ሄደቱ ቀጥሏል

82
አዲስ አበባ ሰኔ 19/2010 ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይን ለመደገፍ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ደም የመለገስ ሄደቱ ቀጥሏል። የሴቶችና የህጻናት ጉዳይ ሚኒስትር ወይዘሮ ያለም ጸጋ ና ሚኒስትር ዴኤታዋ ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ ዛሬ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተገኝተው ደም ለግሰዋል። ሰኔ 16 ቀን 2010ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ለመደገፍ በተደረገው ሰላመዊ ሰልፍ ላይ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት አካላት እና የተለያዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ደም እየለገሱ ሲሆን ዛሬም ሚኒስትሮቹ ይሄንኑ ተግባር ፈጽመዋል። በጉብኝታቸው ወቅትም ከፍተኛ የህክምና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸውና የመታከሚያ አቅም ለሌላቸው ሴቶችና ህጻናት ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል። ደም መለገስ በዘመቻ ብቻ የሚሰራ ተግባር ሳይሆን በተከታታይነት ሊከናወን አንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ለተጎጂዎቹ የአስር ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም